ጥርስ (ማሽን)
From Wikipedia, the free encyclopedia
ጥርስ ተሽከርካሪ ማሽኝ ሲሆን እላዩ ላይ በተቀረጹ ጥርሶች የሌላን አካል ጥርስ በመንከስ ጠምዛዥ ጉልበትን ከአንድ አካል ወደ ሌላ የሚያስተላልፍ ነው። ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ጥርሶች ተባብረው ሲሰሩ አስተላላፊ(ትራንስሚሽን) ይሰኛሉ። ጥርሶች የአንድን ሃይል ምንጭ አቅጣጫ፣ መጠንና ፍጥነት ቀይረው ማስተላለፍ ይችላሉ። ስለሆነም ለመኪና ማርሽነት ግልጋሎት ይሰጣሉ። በጥርስ ቁጥሮች ልክ ትክክለኛ የፍጥነት ውድር መቀመር ስለሚቻል ጥርሶች ለሰዓት ስራ ያገለግላሉ።