From Wikipedia, the free encyclopedia
ተራ ጉሬዛ (ሮማይስጥ፦ Colobus guereza) ኢትዮጵያና አፍሪካ ውስጥ የሚገኝ ዝንጀሮ ነው።
በጉሬዛ ወገን ውስጥ የተዛመዱት ዝርዮች ጥቁር ጉሬዛ (ኢኳቶሪያል ጊኔ ዙሪያ)፣ የአንጎላ ጉሬዛ (አንጎላ፣ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክና ታንዛኒያ)፣ ንጉሥ ጉሬዛ (ሴኔጋል ዙሪያ)፣ ነጭ-ጭን ጉሬዛ (ጋና ዙሪያ) ናቸው። የተዛመዱት ወገኖችም ቀይ ጉሬዛዎችና ወይራ ጉሬዛ ከኢትዮጵያ ውጭ ይገኛሉ። እነዚህ ዝንጀሮች ሁሉ ደግሞ «ኮሎበስ» ተብለው ከሌሎች ዝንጀሮች የሚለዩበት አውራ ጣት በመጎደላቸው ነው። የሚበሉት በተለይ ያልበሰለ ቡቃያ ሲሆን፣ እነዚህ ዝንጀሮች ብቻ የሚያመሰኳ ሆድ አላቸው።
ጉሬዛ በተለይ ቅጠልን እንዲሁም ፍራፍሬን ይበላል፤ አንዳንዴም እንጨት፣ ያትክልት ዘር፣ አበባ፣ አፈርም ወይም ጋጥመ-ብዙ ይበላል።
ጉሬዛ የምግብ ሰንሰለት አካል እንዲሆን የተፈጠረ አውሬ ይመስላል። በተለይ በንሥር እንዲሁም በግስላ ይነጠቃል፤ ከኢትዮጵያም ውጭ ሐለስት ቺምፓንዚ ያድነዋል። ሐለስት ግን ከሁሉ ቀይ ጉሬዛን ይመርጣል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.