ደቡብ ኦሤትያ-አላኒያ (ኢሮንኛ፦ /ኹሣር ኢርስቶን-አሎንስቶን/) በከፊል ተቀባይነት ያገኘ አገር ነው። ነጻነቱን በ1983 ዓ.ም. ያዋጀ ምንም ቢሆን፣ ጂዮርጂያ ግን ይግባኝ አለው።

የደቡብ ኦሤትያ ሥፍራ (አረንጓዴ)

ተባበሩት መንግሥታት የሚከተሉት አገራት ደቡብ ኦሤትያን ተቀባይነት ሰጥተዋል፦ ሩስያኒካራጓ (በ2000 ዓ.ም.) ፤ ቬኔዝዌላ (2001 ዓ.ም.)፣ ናውሩ (2002 ዓ.ም.)፣ ሶርያ (2010 ዓ.ም.)

በከፊል ተቀባይነት ካገኙት ሌሎች አገሮች፣ አብካዝያትራንስኒስትሪያ እና አርጻኽ (የቀድሞው ናጎርኖ-ካራባቅ) ደቡብ ኦሤትያን እርስ በርስ ይቀበላሉ። ምዕራባዊ ሣህራ ደግሞ ደቡብ ኦሠትያን ተቀብሏል።

በተጨማሪ ቱቫሉ ከ2003 እስከ 2006 ዓ.ም. ድረስ ይቀበለው ነበር።

የተረፉት መንግሥታት የጂዮርጂያ ግዛት እንዲሆን የጂዮርጂያን ይግባኝ ተቀባዮች ናቸው።

መጋቢት 2009 ዓም ከተደረገው ሕዝቡ ውሳኔ ቀጥሎ የሀገሩ ስም በይፋ ከ «ደቡብ-ኦሤትያ» ወደ «ደቡብ-ኦሤትያ-አላኒያ» ተቀየረ። የአገሩ ሕዝብ ከታሪካዊ አላኖች ብሔር እንደ ተወለደ ይታመናል፤ ታሪካዊውም አላኒያ ከ890-1230 ዓም ያሕል በአካባቢው የቆየ መንግሥት ነበረ።


Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.