ያዕቆብ

From Wikipedia, the free encyclopedia

ያዕቆብ

ያዕቆብ (ዕብራይስጥ፦ יַעֲקֹב, /የዕቆብ/) በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት የይስሐቅና የርብቃ ልጅ ነበረ። የዔሳው መንታ ወንድም ነበር። በሌላ ስማቸው ኤዶምያስ (ዔሳው)ና እስራኤል (ያዕቆብ) የተባሉትን ሁለት ብሔሮች ወለዱ። ያዕቆብ (እስራኤል) ግን የተቀደሠ የመሢህ ዘር ተስፋ ወራሽ ሆነ። ያዕቆብና ሚስቶቹ ከነቁባቶቹ የእስራኤል ፲፪ ነገዶች ወለዱ።

Thumb
ያዕቆብ - የሩስያ ኦርቶዶክስ ስዕል፣ 1720 ዓ.ም. ግድም ተሳለ

ዕዝራ ሱቱኤል ምዕ. ፬ በአዋልድ መጻሕፍት ዕዝራ የዚህን አለም መጨረሻ ከእግዜር መንግሥት መጀመርያ ምን ይለየዋል ሲጠይቅ፣ መልዐኩ ያዕቆብ ከኤሳው ቀጥሎ እንደ ወጣ (ቅርጭምጭሚት ተጨብጦ) ይከተላል የሚል መልስ ሰጠ።

የያዕቆብ ታሪክ በተለይ የሚታወቀው ከብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘፍጥረት ነው። በተጨማሪ መጽሐፈ ኩፋሌ ስለ ያዕቆብ ሕይወት ብዙ ይጻፋል።

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.