የአክሱም ሐውልት
አክሱም ትግራይ / From Wikipedia, the free encyclopedia
የአክሱም ሃውልት (እንግሊዝኛ: Obelisk of Axum) ወይም Rome Stele እየተባለ በተለምዶ የሚጠራው በኢትዮጲያ በአክሱም ከተማ የሚገኝ የአለማችን ረጅሙ ትክል ድንጋይ ሃውልት ነው። ይህ ሀውልት 1700 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን የ24 ሜትር (78 ጫማ) ርዝመት አለው። 160 ቶን የሚመዝነው ይህ ግዙፍ ድንጋይ መሠረቱ አከባቢ ሁለት የሀሠት በር መሣይ ፍልፍሎች አሉት። የዚህ ሀውልት ጌጥ ይህ ብቻም አይደለም በያንዳንዱ ጎን የመስኮት ቅርጽ የያዙ ፍልፍሎች ሲኖሩት በመጨረሻው ጫፍ ላይ ደግሞ በብረት ፍሬም የታገዘ የግማሽ ክብ ነው::