![cover image](https://wikiwandv2-19431.kxcdn.com/_next/image?url=https://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/b/be/Narmer_Palette.jpg/640px-Narmer_Palette.jpg&w=640&q=50)
የናርመር መኳያ ሠሌዳ
From Wikipedia, the free encyclopedia
የናርመር መኳያ ሠሌዳ ከጥንታዊ ግብጽ መጀመርያ ፈርዖን ወይም አምባ ገነን ከናርመር ዘመን (3100 ዓክልበ. ግድም) የታወቀ ጥንታዊ ኩል መኳያ ቅርስ ነው።
![Thumb image](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/b/be/Narmer_Palette.jpg/640px-Narmer_Palette.jpg)
የኩል መኳያ ሠሌዳ በጥንታዊ ግብጽ መጀመርያ ኩልን (ለዓይን ቆብ ኮስሞቲክ) ለማዘጋጀት የጠቀመ እቃ ነበር። የኩል መኳያ ሠሌዶች የሚታወቁ በተለይ ከናርመር ዘመንና ከናርመር ጥቂት አስቀድሞ በሆነው ዘመን ብቻ ነው («ቅድመ-ሥርወ መንግስት»፣ በንጉሥ ጊንጥ ዘመን ያህል ነው) ። ከናርመር ዘመን ቀጥሎ ግን የኩል መኳያ በግብጽ በብዛት አልተሠራም ነበር።
ቅርሱ በ1890 ዓም በነቀን ከተማ ተገኘ። እድሜው ከ፭ ሺህ አመታት በላይ ቢሆንም ሁኔታው በጣም ደህና ነው። የተቀረጸውም ከድቃቅ አሸዋ ድንጋይ ነው።
በዚህ ታዋቂ ናሙና ላይ፣ በያንዳንዱ ጎን ላይ በላይኛ ጫፍ የናርመር ስም በሃይሮግሊፍ ጽሑፍ ናር-መር ከሁለት በሬ ራሶቹ መካከል ይታያል።