From Wikipedia, the free encyclopedia
ዛሬማ ጊዮርጊይስ ከአጽቢ ሰሜን 20 ኪሎሜትር ላይ ባለው የዛሬማ መንደር የሚገኝ ጥንታዊ ቤተክርስቲያን ነው። ቤተክርስቲያኑ ሁለት ክፍል ሲኖረው፣ የመጀመሪያው ክፍል የውጨኛው ህንጻ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ይተሰራና ውስጡ ያለውን ህንጻ የሚደብቅ ነው። ይሄው ክፍል አጠቃላይ ስፋቱ (13.70 mx 8.90 m) ሲሆን በሳር የተሸፈነ ጣሪያና ብዙም እንግዳ ያልሆነ ግድግዳ አለው። ሁለተኛውና በውስጥ ተደብቆ የሚገኘው ቀደምት ቤተክርስቲያን ሲሆን የተገነባውም ከ9-13ኛው ክፍለ ዘመን ባለው ጊዜ ውስጥ ነበር[1]። በውጭውና በውስጡ መካከል ያለው ክፍተት እንደ ቅኔ ማህሌት ሲያገልገል ውስጠኛው አሮጌው ቤተክርስቲያ እንደ መቅደስ ያገለግላል። ውስጠኛው ቤተክርስቲያን እጅግ ብዙ በሆኑ ቅርጻቅርጾች ያሸበረቀና፣ ኢትዮጵያ ከሚገኙ አብያተክርስቲያናት ለየት ባለ መልኩ ሁለት አጥቢያ እና አጠቃላይ አቅዱ የመስቀል ቅርጽ ያለው ነው። አስራሩም እንደ ደብረ ዳሞ እና ይምርሃነ ክርስቶስ፣ በግንዶችና ጥርብ ድንጋዮች ንብብር ነው[2]። ሆኖም ግን፣ ከነዚህ ለየት ባለ መልኩ አቋራጭ ግንድ እና የዝንጀሮ እራስ እሚባሉት የአክሱማዊ ህንጻ አሰራር ዘዴዎች በዚህ ቤተክርስቲያን አይታዩም[3]። ታሪክ አጥኝው ለፔጅ ክላውድ፣ ከዚህ በመነሳት የዛሬማ ጊዮርጊስን ግንባታ በደብረ ዳሞ እና ይምርሃነ ክርስቶስ መካከል ያስቀምጠዋል።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.