![cover image](https://wikiwandv2-19431.kxcdn.com/_next/image?url=https://upload.wikimedia.org/wikipedia/am/thumb/5/52/GuzaraCastle1.jpg/640px-GuzaraCastle1.jpg&w=640&q=50)
ሠርፀ ድንግል
From Wikipedia, the free encyclopedia
ዓፄ ሠርጸ ድንግል ( 1542 - መስከረም 27, 1590 ) በዙፋን ስማቸው "መለክ ሰገድ" ኢትዮጵያን ከ1555 - 1590 ዓ.ም. የመሩ ንጉሥ ነበሩ። አባታቸው ዓፄ ሚናስ ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ እቴጌ አድማስ ሞገስ ነበሩ። ከግራኝ ወረራ ጀምሮ እስከ ዓፄ ሚናስ ዘመን የቀጠለው አለመረጋጋት በኒህ ንጉሥ ዘመን አንጻራዊ እልባት አግኝቷል። ለዚህ ተጠያቂ የሚሆኑ አራት ጉልህ ክስተቶች፡ ፩) በሰሜን የቱርኮች ወረራ በንጉሡ ወታደራዊ ብቃት በመክሸፉ ፪) በደቡብ የባሬንቱ ኦሮሞዎች ሐረርን በመውረራቸው የአዳል ግዛት ኃይል በመዳከሙ እና ስለዚህ ምክንያት ከአዳል ጦርነት በማብቃቱ ፫) የቦረና ኦሮሞዎች ወደ ሸዋ የሚያካሂዱትን ዘመቻ ለጊዜው መግታት በመቻሉ፣ ፬) የአገሪቱን ዋና ከተማ ከመካከለኛው ክፍል ወደ አባይ ምዕራብ በማሻገሩ ነበር[1]። በአጠቃላይ መልኩ ይህ ንጉስ ከሚናስ የተረከበውን ግዛት አስፍቶና አጠናክሮ ለቀጣዩ መሪ ትቶ አልፈዋል። የንግሱ ባለቤት እቴጌ ማርያም ሰናም ለተከታዮቹ ነገሥታት መነሳትም ሆነ መውደቅ ባበረክተችው አስተዋጽኦ በታሪክ ትታወሳለች።
==
Quick Facts ዓፄ ሠርጸ ድንግል, ግዛት ...
ዓፄ ሠርጸ ድንግል | |
---|---|
![]() | |
በ1571 ዓፄ ሠርፀ ድንግል የገነቡት የጉዛራ ቤተ መንግስት፣ በእምፍራዝ፣ | |
ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ | |
ግዛት | ከ1555 እስከ 1589 እ.ኤ.አ. |
ቀዳሚ | ዓፄ ሚናስ |
ተከታይ | ዓፄ ያዕቆብ |
ባለቤት | ንግሥት ማርያም ሰና |
ሙሉ ስም | መልአክ ሰገድ (የዙፋን ስም) |
ሥርወ-መንግሥት | ሰሎሞን |
አባት | ዓፄ ሚናስ |
እናት | አድማስ ሞገሴ |
የተወለዱት | 1542 |
የሞቱት | 1589 |
የተቀበሩት | መድሀኒ ዓለም ቤተ ክርስቲያን፤ ሬማ ደሴት |
ሀይማኖት | የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና |
Close
==