ጥቅምት ፳፭
- ፲፰፻፹፪ ዓ.ም - የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ በ እንጦጦ “መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም” ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሊቀ ጳጳሱ በአቡነ ማቴዎስ እጅ ቅብዓ መንግሥት ተቀብተው፣ ዳግማዊ ምኒልክ ተብለው የንጉሠ ነገሥት ዘውድ ጫኑ።
- ፲፱፻፲፭ ዓ.ም.- በግብጽ የጥንታዊ ፈርዖን ቱቴንኻሙንን የመቃብር ቤት (pyramid) መግቢያ በር የእንግሊዝ ተወላጁ ሃዋርድ ካርተር አገኘ።
- ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. - የኢራን ሻህ ሬዛ ፓህላቪ በሕዝብ ፍንቀላ ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ አብዮታዊ ተማሪዎች የአሜሪካን ኤምባሲ በኃይል ደምሥሠው ገብተው ዘጠና የአሜሪካ ዜጎችን በቁጥጥራቸው ስር አዋሉ።
- ፲፱፻፹፰ ዓ.ም - በእስራኤል የአክራሪ ኦርቶዶክስ ቡድን አባል ጠቅላይ ሚኒስቴሩን ይስሐቅ ራቢንን በዓደባባይ ገደለ።
- ፳፻፩ ዓ.ም. - በአሜሪካ የፕሬዚዳንታዊ ውድድር ባራክ ኦባማ የመጀመሪያው ጥቁር አሜሪካዊ ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ።