ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/መጋቢት 26
From Wikipedia, the free encyclopedia
- ፲፰፻፺፯ ዓ/ም - ‘የካንግራ ሸለቆ’ በሚባለው የሕንድ ግዛት ውስጥ የተከሰተው እሳተ ገሞራ የ ፳ ሺ ሰዎችን ሕይወት ሲያጠፋ የአካባቢውን ከተማዎችና ሠፈሮች አውድሟል።
- ፲፱፻፵፩ ዓ/ም - አሥራ ሁለት ምዕራባውያን አገሮች፤ የአሜሪካ ኅብረት፣ ታላቋ ብሪታንያ፣ ፈረንሲስ፣ ቤልጂግ፣ ሆላንድ፣ ዴንማርክ፣ ኢጣልያ፣ ሉክሳምቡርግ፣ ኖርዌይ፣ አይስላንድ፣ ካናዳ እና ብርቱጋል በስምምነት የሰሜን አትለንቲስ የውል ድርጅት (North Atlantic Treaty Organization (NATO) ) መሠረቱ
![Thumb image](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/8/84/Martin_Luther_King_Jr_NYWTS.jpg/640px-Martin_Luther_King_Jr_NYWTS.jpg)
- ፲፱፻፷ ዓ/ም - በአሜሪካ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና የጥቁር አሜሪካውያን መሪ የነበረው ታናሹ ማርቲን ሉተር ኪንግ ጄምስ ኧርል ሬይ በተባል ነፍሰ ገዳይ እጅ በሜምፊስ ከተማ ተገደለ። የኪንግ ሞት ዜና ሲሰማ በ መቶ የአሜሪካ ከተሞች ከፍ ያለ የሕዝብ ሽብር ተከተለ።