![cover image](https://wikiwandv2-19431.kxcdn.com/_next/image?url=https://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/3/30/Venn0111.svg/langam-640px-Venn0111.svg.png&w=640&q=50)
ውህድ ስብስብ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ሁለት ስብስቦች "ሊደመሩ" ይችላሉ። መደመርን መተግብሪያ ውህድ ስብስብ ሲሆን፣ የA እና B ውህድ እንዲህ ይጻፋል A ∪ B ። ትርጓሜውም በ A ወይም በ B የሚገኙ ሁሉም አባላት ስብስብ ማለት ነው።
![](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/3/30/Venn0111.svg/320px-Venn0111.svg.png)
የ A እና Bውህድ እንዲህ ይወከላልA ∪ B
ምሳሌ:
- {1, 2} ∪ {ቀይ, ነጭ} ={1, 2, ቀይ, ነጭ}
- {1, 2, አረንጓዴ} ∪ {ቀይ፣ ነጭ፣ አረንጓዴ} ={1, 2, ቀይ፣ ነጭ፣ አረንጓዴ}
- {1, 2} ∪ {1, 2} = {1, 2}
አንድ አንድ መሰረታዊ የውህድ ስብስብ ጸባዮች:
- A ∪ B = B ∪ A.
- A ∪ (B ∪ C) = (A ∪ B) ∪ C.
- A ⊆ (A ∪ B).
- A ∪ A = A.
- A ∪ ∅ = A.
- A ⊆ B if and only if A ∪ B = B.
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |