ቢግ ማክ የሃምበርገር ዓይነት ሲሆን በፈጣን ምግብ ቤቱ ማክዶናልድስ የሚሸጥ ነው። ሃምበርገሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረው በ1960 ዓ.ም. በአሜሪካኑ ጅም ዴልጋቲ ነበር። ሁለት የተፈጨ የበሬ ስጋ ክቦችን፣ ሰላጣ ቅጠል፣ ዓይብ፣ ሽንኩርት፣ ፒክልስ እና ሶስት የሰሊጥ ጠፍጣፋ ዳቦዎችን ከማዋዣ የቢግ ማክ ሶስ (መረቅ) ጋር ይይዛል።
ቢግ ማክ በኣሁኑ ዘመን በአለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተዎዳጅነትን በማግኘቱ ዘ ኢኮኖሚስት የተሰኘው የሥነ ንዋይ ጋዜጣ በያመቱ ቢግ ማክ ኤንዴክስ የተባለ መረጃ ያትማል። ቢግ ማክ በያገሩ የሚሸጥበትን ዋጋ በማዎዳደር፣ የየአገሩን የኑሮ ውድነት ለማነጻጻር ይጠቀምበታል። |
|
|
ታሪክ በዛሬው ዕለት (ሜይ 9, 2024 እ.ኤ.አ.):
- ፲፰፻፵፬ ዓ/ም - ራስ መኮንን ከ ልዕልት ተናኘወርቅ ሣህለ ሥላሴ እና ከደጃዝማች ወልደሚካኤል ወልደ መለኮት ጎላ ወረዳ ደረፎ ማርያም በሚባል ሥፍራ ተወለዱ።
- ፲፱፻፳፰ ዓ/ም - የኢጣልያ ንጉሥ ቪክቶርዮ ኢማኑኤል ሣልሣዊ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ እና ግዛት በኢጣልያ አስተዳደር ሥር የሚያደርግ አዋጅ አስንገረው፣ ይሄንኑ አዋጅ ለዓለም መንግሥታት እንዲሰራጭ አዘዙ። የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥትነት ማዕርግ ከዚህ ዕለት ጀምሮ የእሳቸውና የወራሾቻቸው እንደሆነ፣ የኢትዮጵያም ሕዝብ እና ግዛት በእንደራሴ እንደሚታደደር በዚሁ አዋጅ ይፋ ተደርገ።
- ፲፱፻፴፯ ዓ/ም - የኢጣልያ ንጉሥ ቪክቶርዮ ኢማኑኤል ሣልሣዊ፣ ከዙፋናቸው ወርደው ዘውዱ ወደንጉሥ ዳግማዊ ኡምቤርቶ ተዛወረ።
- ፲፱፻፺፫ ዓ/ም - በጋና ርዕሰ ከተማ አክራ የእግር ኳስ ሜዳ በሚካሄድ ጨዋታ ላይ ተመልካች ሕዝብ በዳኛው ውሳኔ ባለመስማማቱ የተነሳውን ረብሻ ለማብረድ፣ ፖሊሶች የተኮሱት የጢስ ቦምብ ሕዝቡን የባሰውን ሲያተራምሰው በተከሰተው ትርምስና የሰው ግፊያ ፻፳፱ ሰዎች ተጨፍልቀው ሕይወታቸውን አጡ።
|
|