From Wikipedia, the free encyclopedia
ኤፍሮን ኬጢያዊው (ዕብራይስጥ፦ עפרון החתי /ዔፍሮን ኸሔቲ/) በኦሪት ዘፍጥረት 23 ዘንድ የሰዓር ልጅ ሲሆን ከኬጢ ልጆች (ኬጥያውያን) አንድ ነበር። በመምሬ፣ ከነዓን አገር ይኖር ነበር። በኬብሮን ያለውን ድርብ ክፍል የሆነውን ዋሻ ለአብርሃም ለ፬ መቶ የብር ሰቅል ሸጠው። ይህ የአብርሃም ሚስት ሣራ ባረፈችበት ጊዜ መቃብር እንዲሆንላት ነበር።
አብርሃም በዙሪያው በኩል የገነነ የከበረ ስለ ሆነ፣ የኬጢ ሰዎችና ኤፍሮንም ዋሻውን በነጻ ለአብርሃም ይሰጡት ነበር። አብርሃም ግን ባለጠጋና ጽድቅ ሆኖ ትክክለኛ ዋጋ ኢንዲከፍል ኤፍሮንን አጥብቆ ይጠይቀዋል። ይህ ዋሻ በዕብራይስጡ «መክፔላህ» ይባላል፤ ይህም «ባለ ድርብ ክፍል» ማለት ነው።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.