ኤላም
From Wikipedia, the free encyclopedia
ኤላም ጥንታዊ ሃገር ነበር። ዛሬ ደቡብ-ምዕራብ ፋርስ በሆነ አቅራቢያ ተገኘ። መነሻው በዋና ከተማው በሱስን (ሹሻን) እና በካሩን ወንዝ ሸለቆ ከታሪክ መዝገብ መጀመርያ ሲሆን እስከ 547 ክ.በ. ድረስ ቆየ። ከሱመር እና ከአካድ (የዛሬ ኢራቅ) ወደ ምስራቅ የሆነ አገር ነበር። የኤላም መንግሥት ለፋርስ ከወደቀ በኋላ ቢሆንም የኤላም ቋንቋ በፋርስ አሐይመንድ መንግሥት በመደብኝነት ቆይቶ ነበር። ይህ ቋንቋ የፋርስኛ ዘመድ ሳይሆን ምናልባት ለደቡብ ሕንድ ድራቪዲያን ቋንቋዎች የተዛመደ ይሆናል።
![Thumb image](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/1/12/Elam_Map.jpg/220px-Elam_Map.jpg)
እስከ ዛሬም ድረስ በፋርስ አገር ውስጥ ኢላም ክፍላገር ከጥንታዊው አገር ተሰይሞ ይገኛል።
ኤላማውያን የራሳቸውን ሀገር ስም ሃልታምቲ ብለው ሰይመውት ሲሆን ለጎርቤቶቻቸው ለአካዳውያን «ኤላምቱ» በመባል ታወቁ። 'ኤላም' ማለት 'ደጋ' ሊሆን ይቻላል። ከዚህ በላይ በብሉይ ኪዳን (ዕብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ) አገሩ 'ኤላም' ተብሏል፤ ስሙም ከኖኅ ልጅ ሴም ልጅ ኤላም ነው።