ኢሎካኖኛ (Ilocano) በተለይ በፊልፒንስ ሉዞን ደሴት የሚነገር ቋንቋ ነው። የኢሎካኖ ብሔር ኗሪ ቋንቋ ነው።
ስፓንያውያን ከደረሱ በፊት ቋንቋው የራሱን አቡጊዳ ነበረው። ዛሬ ግን የሚጻፍበት በላቲን ጽሕፈት ነው። ከተለመዱት 26 ፊደላት ጭምር (Ñ ñ - ኝ) እና (NG ng - ጝ) ከ (N n) ቀጥለው ተሳክተው እንደ ሁለት ተጨማሪ ፊደላት ይቆጠራሉ፤ በጠቅላላ የኢሎካንኛ ፊደል 28 ፊደላት ይቆጥራል።
አንዳንድ ቃላት ከእስፓንኛ፣ እንግሊዝኛ፣ አረብኛ፣ ሳንስክሪትና ቻይንኛ ተበድረዋል።