ኡልትራ አጭር አቆጣጠር
From Wikipedia, the free encyclopedia
From Wikipedia, the free encyclopedia
ኡልትራ አጭር አቆጣጠር (አብልጦ አጭር አቆጣጠር) ማለት በታሪክ ሊቃውንት ከተገመቱት የጥንት (ከ1000 ዓክልበ. በፊት) ዘመን አቅጣጠሮች መካከል አንዱ ነው።
ከ1000 ዓክልበ. ያሕል በኋላ ለሆነው ታሪክ፣ በተወሰነ አመት ይህ ድርጊት ሆነ ለማለት በጣም አጠያያቂ አይደለም። ከዚያ አስቀድሞ ግን መዝገቦች በካሳውያን ዘመን ጥቂት ስለ ነበሩ፣ ትንሽ 'ጨለማ ዘመን' ተብሏል። በ«ኡልትራ አጭር አቆጣጠር» ዘንድ፣ በ1507 ዓክልበ. የሐቲ (የኬጥያውያን) ንጉስ 1 ሙርሲሊ ባቢሎንን ዘረፈ፤ ከዚያ ካሳውያን ከተማውን ይዘው ስሙን ካራንዱንያሽ አሉት።
የባቢሎን መጨረሻ ንጉሥ ሳምሱ-ዲታና ለ31 ዓመታት የነገሠ ቢታወቅም፣ የባቢሎን (ካርንዱንያሽ) መጀመርያ ካሳውያን ነገሥታት (እስከ 1 ካዳሽማን-ኤንሊል ድረስ፣ 1383-1368) ግን ስንት አመታት እንደ ነገሡ በትክክል ስላልተገኘ፣ የባቢሎን ውድቀት አመት በትክክል ለመወሰን ለረጅም ጊዜ አልተቻለም ነበር። ዳሩ ግን በንጉሥ አሚ-ሳዱቃ ዘመን በ8ኛው ዓመት የዘሃራ ሁኔታና አቀማመጥ በደንብ ስለ ተመዘገበ፣ ይህ የታሪክ ሊቃውንት ዘመኑን ለመወሰን ረድቷል። ስለዚሁ የሥነ ፈለክ ቁጠራ፣ የአሚ-ሳዱቃ 8ኛው አመት ወይም በ1702፣ በ1646፣ በ1582፣ ወይም በ1550 ዓክልበ. እንደ ተከሠተ ታወቀ። ዛሬ የብዙ አገራት ታሪክ ሊቃውንት «መካከለኛ አቆጣጠር» የተባለውን ሲቀበሉ፣ የአሚሳዱቃ 8ኛው አመት በ1646 እና የባቢሎን ውድቀት በ1603 ዓክልበ. የሚወስኑት ናቸው። አለዚያ «አጭር አቆጣጠር» ተከትለው የአሚሳዱቃ 8ኛው አመት በ1582፣ የባቢሎንም ውድቀት በ1539 ዓክልበ. ያደርጉታል።
ባለፈው ቅርብ ጊዜ ግን በሥነ ቅርስ እርምጃ ሳቢያ የአሦር ነገሥታት ዘመናት ቁጥር ለማወቅ ስለ ተቻለ፣ የፈረንሳይ ሊቅ ዤራርድ ዠርቱ «ከሁሉ አጭሩ» ('ኡልትራ' ወይም 'አብልጦ አጭር') አቆጣጠር በትክክል እንደሚስማማው አስረድቷል።[1] የአሚሳዱቃ 8ኛው አመት በ1550፣ የባቢሎንም ውድቀት በ1507 ዓክልበ. ሆነ (ወይም ክ.በ. በ1499 እንደ ኤውሮጳውያን አቆጣጠር) ለማለት እንችላለን ማለት ነው።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.