አስዩት
From Wikipedia, the free encyclopedia
አስዩት (የግብጽ አረብኛ፦ أسيوط /ኣስዩጥ/፤ ጥንታዊ ግብጽኛ፦ /ዛውቲ/፤ ጥንታዊ ግሪክኛ፦ Λυκόπολις /ሊውኮፖሊስ/) የጥንታዊ ግብጽ ከተማ ነበር። ዘመናዊው ከተማ በአጠገቡ ሲሆን ከ6 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች አሉት።
በሄራክሌውፖሊስና በጤቤስ መካከል በተደረገው ብሔራዊ ጦርነት (2107-2081 ዓክልበ. ግድም) የአሥዩት ገዦች ተፊቢ እና ልጁ ቀቲ ለሄራክሌውፖሊስ ፈርዖን መሪካሬ ታማኝ ሆነው በጤቤስ ግዛት ላይ እንደ ዘመቱ ይታወቃል። በመጨረሻ ግን የጠቤስ ፈርዖን 2 መንቱሆተፕ አሸነፈው።