አስዋን ግድብ
From Wikipedia, the free encyclopedia
የአስዋን ግድብ ደቡባዊ የግብፅ ከተማ በሆነችው አስዋን ውስጥ የሚገኝ የናይል ትልቅ ግድብ ነው። ከ1950ዎቹ እ.አ.አ. ጀምሮ ሥሙ የሚገልፀው ከፍተኛው ግድብ የሚለውን ሲሆን ይህም በ1902 እ.አ.አ. የተጠናቀቀውን የአስዋን ዝቅተኛ ግድብ አዲስ እና ታላቅ መሆኑን ለማሳየት ነው። ከ1960 እስከ 1970 እ.አ.አ. ነበር ከእንግሊዝ የሀገሪቱን ቅኝ ግዛት ነፃ መሆን ተከትሎ የዚህ ግድብ ግንባታ የተካሄደው። የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ከማሳደግ አንጻር ከፍተኛ ሚና እንዲጫወት ተደርጎ የተገነባው ይኸው ግድብ ከአላስፈላጊ የጎርፍ አደጋዎች ለመጠበበቅ፣ ለግብርና የሚውል የውሃ ክምችት እንዲኖር በማድረግ በመጨረሻም በቂ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲኖር ለማድረግ አስችሏል። ኡህ ግድብ ለግብፅ ምጣኔ ሃብታዊ እድገት እና ባህል ከፍተኛ አስተዋፅዖ አለው።
ከግድቡ መገንባት በፊት ባሉት ዓመታት አካባቢው በተደጋጋሚ የወንዝ ሙላት ያጋጥም ነበር። በዚህ ሙላት የተለያዩ ማዕድናት ከምስራቅ አፍሪካ የወንዙ ምንጭ ሀገራት ተጠራርጎ ይመጣል። ይህም የናይል ወንዝ አካባቢን ከጥንታዊ ግብፆች ጀምሮ ለግብርና ምቹ ያደርገዋል። ይህ የወንዝ ሙላት በጣም ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ የተተከሉ አዝዕርቶችን እንዳለ ጠራርጎ ሊወስድ ይችላል። እንዲሁም ወንዙ በጣም ዝቅ በሚልበት ወይም በሚደርቅበት ጊዜ ደግሞ ድርቅ እና ረሃብ በአካባቢው ይከሰታል። በአሁኑ ጊዜ ግን የሀገሪቱ የህዝብ ቁጥር በመጨመሩ እና እነዚህን መሰል አደጋዎች የመከላከል እና የመቋቋም ብቃቱን እያዳበረች በመምጣቷ ለጥጥ ምርት ተጨማሪ ውሃ ማጠራቀም ተችሏል። ይህም የተጠራቀመ ውሃ የወንዙ መድረቅ በሚከሰትበት ጊዜ ጥቅም ላይ ይውላል።