አርጌንቶማጉስ
From Wikipedia, the free encyclopedia
አርጌንቶማጉስ በሮሜ መንግሥት ዘመንና ከዚያም በፊት የጋሊያ (አሁን ፈረንሳይ አገር) ከተማ ነበር። ቢቱሪጌስ የተባለ ጎሣ በዙሪያው ይኖር ነበር። 42 ዓ.ም. አካባቢ ሮማውያን ያዙት። ፍርስራሹ ከዛሬው አርዠንቶን-ሱር-ክሮይዝ አጠገብ ይገኛል።
Quick Facts አርጌንቶማጉስ ...
Close
አርጌንቱም ማለት «ብር» ሲሆን የማጉስ ትርጉም «ገበያ» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚያ ዘመን አያሌ ገበዮችና መንደሮቹ «-ማጉስ» በሚለው ስም ይጨረሱ ነበር። በአንድ ትውፊት ግን ማጉስ ከተሞቹን የመሠረተው የጥንት ንጉሥ ስም ነበረ።