አማ አታ አዪዶ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ክሪስቲና አማ አታ አዪዶ በማርች 23፣ 1942 እ.ኤ.አ. ጋና ውስጥ ተወለደች። ትምህርቷን በዌስሊ የልጃገረዶች ትምህርት ቤት፣ በመቀጠልም በጋና ዩኒቨርስቲ ተከታትላ በ1964 ዓ.ም በእንግሊዝኛ ቋንቋ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ተቀብላለች። የመጀመሪያ የድርሰት ስራዋ የሆነውን «The Dilemma of a Ghost»ን በዚያ ዓመት ለማጠናቀቅ የበቃች ሲሆን ይሄው ድርሰቷ በሎንግማን አሳታሚ ድርጅት አማካይነት በቀጣዩ ዓመት ታትሞላታል።
![Thumb image](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/am/f/f1/Ama_ata_aidoo.jpg)
አዪዶ በልብ-ወለድ ደራሲነት ብቻ አይደለም እውቅናን ያተረፈችው፤ በጸሃፌ-ተውኔትነት እና ገጣሚነትም እንጂ። ጽሁፎቿ በአብዛኛው የዘመኑ የአፍሪካ ሴቶች ስላላቸው ሚና እና የምእራባዊው ባህል ስለሚያሳድርባቸው ኢርቱእ ተጽኖ ላይ የሚያተኩሩ ናቸው።
አዪዶ በ1982 የጋና የትምህርት ሚኒስትር ሆና ብትሾምም በስራው ላይ የቆየችው ለ18 ወራት ያህል ብቻ ነው። በአሁኑ ወቅት በብራውን ዩኒቨርስቲ የአፍሪካ ጥናት ክፍል ውስጥ ተጋባዥ ፕሮፌሰር በመሆን ትሰራለች።