From Wikipedia, the free encyclopedia
ኒው ዚላንድ በደቡብ ምዕራብ ፓሲፊክ ውቅያኖስ የምትገኝ የደሴት ሀገር ናት።
ኒው ዚላንድ |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ኒው ዚላንድ በአረንጓዴ ቀለም
|
||||||
ዋና ከተማ | ዌሊንግተን | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | እንግሊዝኛ፣ ማዎሪ፣ የምልክት ቋንቋ | |||||
መንግሥት {{{ ንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር |
ግርማዊት ንግሥት ኤልሳቤጥ ፪ኛ ጆን ኪይ |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) |
268,021 (74ኛ) 2.1 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2010 እ.ኤ.አ. ግምት የ2006 እ.ኤ.አ. ቆጠራ |
4,367,700 (123ኛ) 4,027,947 |
|||||
ገንዘብ | የኒው ዚላንድ ዶላር | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +12 | |||||
የስልክ መግቢያ | +64 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን | .nz |
በኒው ዚላንድ በዋንነት የሚነገረው መደበኛ ቋንቋ እንግሊዝኛ ነው። ማዖሪኛ በተለይ በማዖሪ ብሔር ይነገራል፣ በ1979 ዓ.ም. ደግሞ ይፋዊ ቋንቋ ሆነ። ከ1998 ዓ.ም. ጀምሮ የአገሩ ሦስተኛው ይፋዊ ቋንቋ የኒው ዚላንድ እጅ ምልክት ቋንቋ ሆኗል።
ከኒው ዚላንድ ሕዝቦች መካከል የማዖሪ ብሔር ከሁሉ ይልቅ ለረጅም ዘመን በደሴቶቹ ላይ ኑረዋል። ማዖሪዎች «ሃካ» ስለ ተባለው ባህላዊ የውግያ ጭፈራ ታውቀዋል። በኒው ዚላንድ ባሕል ደግሞ የአገሩ ስፖርት (በተለይ የራግቢ) ቡድኖች ጨዋታ ሳይጀምሩ ሁልጊዜ «ሃካ» ይጨፍራሉ።
አንዳንዴ በቀልድ የኒው ዚላንድ ባህል ዓምዶች «ሦስቱ Rዎች» ይባላሉ - እነሱም «Rugby Racing እና beeR» (ራግቢ፥ እሽቅድድምና ቢራ) ናቸው። እንዲያውም የፈረስ እሽቅድድም አሁን እንደ ቀድሞ ደረጃ የተወደደ አልቆየም፣ ራግቢ እና ቢራ ግን ዛሬውንም በኒው ዚላንድ ሕዝብ በኩል በጣም የሚወደዱ ሆነው ቀርተዋል።
የኒው ዚላንድ ሰዎች አንዳንዴ በመጫወት ሲሆን በራሳቸውም ሆነ በሌሎች ዘንድ «ኪዊዎች» ይባላሉ። «ኪዊዎች» በተለመደው (በጅምላ አመለካከት) ተጨባጭ ያልሆነ ኀልዮ ወይም አሣብ ሳይሆን ተግባራዊ ጉብዝና እና ሙያ ይመርጣሉ። ኒው ዚላንድ ለረጅም ዘመን በክፍሎች ያልተመደበ ሕብረተሰብ ይቆጠር ነበር - ከሃብታሞችና ደሃዎች ኒው ዚላንድ ኗሪዎች መካከል የነበረው ልዩነት ያንስ ነበር ማለት ነው። በቅርቡ ባለፉት አሥርታት ግን ይሄው ሁናቴ ተቀይሯል።
ብዙ የዚው ዚላንድ ኗሪዎች አድገው ወደ ውጭ አገሮች ይጎበኛሉ፣ ብዙዎቹም የባህላዊ ልውውጥ ፕሮግራሞች ይጠቅማሉ፣ ስለዚህ በዓለም ዙሪያ ይገኛሉ፣ በተለይም በአውስትራሊያ፣ ብሪታንያ፣ አውሮፓና እስያ ይጓዛሉ።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.