From Wikipedia, the free encyclopedia
ኑግ በሮማይስጥ Guizotia abyssinica በመባል የታወቀው የእህል ዘር የሚሰጥ ተክል ዝርያ ነው። ኑግ ዩናይትድ አስቴትስ ውሱጥ ተወዳጅ የወፍ ምግብ ነው። ይህን የዘይት እህል በብዛት የሚያመርቱ ኣገሮች ኢትዮጵያና ሕንድ ናቸው ይባላል፣ ሌሎችም አሉ።
ወፎች ስለሚወድዱት ብዙ አገሮችም ያስገቡታል። ዘሩ ወደ ሌላ አገር ሳይገባ ግን የአረም ዘሮች ስላሉበት ስንኩል እንዳይሆኑ ለ15 ደቂቃ በከፍተኛ ሙቀት እንዲቆይ ይገደዳል።
በደቡብ ሕንድ ምግብ አበሳሰል በወጥ ወይም ስጎ ውስጥ ይጨመራል።
የኑግ ዘይት፣ ቅባኑግ ደግሞ ያስገባሉ፤ ለአበሳሰል በወይራ ዘይት ፈንታ ሊጠቀሙ ይችላሉ፣ ወይም ሳሙና፣ ቀለም መቀብያ ለማዘጋጀት ለኢንዱስትሪዎች ይጠቀማል። በተለይ በኢትዮጵያ ቅባኑግን ከማውጣት የተረፈው የዘሩ እንጐቻ ለከብት መኖ ይሰጣል።
በኢትዮጵያ በተቆለለና በደቀቀ ኑግ ውጥ በስኳርና በውሃ ጉንፋን በማከም ይጠቀማሉ። የደቀቀ ኑግና ተልባ ተዋህዶ ቆዳን በመቀባት ለቆዳ ውበትና ጤና ይጠቅማል። ኑግና ጥቁርአዝሙድ ተፈጭቶ ከዝንጅብል ጋር በማዋሃድ በጁስ መልክ በሁለትኩባያ ውሃ ይፈጭና በማጥለያ አጥልሎ ጭማቂውን በቀን አንዴ በመጠጣት የደምግፊትን፣የስኳርበሽታንእንዲሁም የሆድ ቦርጭን ለመቀነስ ይጠቅማል። ኑግ ለጤና እጅግ ጠቃሚ ነው። እንዲሁም የኑግና የመተሬ ዘር ተዋህዶ ለኮሶ በሽታ ይሰጣል። ቁንጭር (ሌይሽመናይሲስ) ለማከም የኑግ፣ የነጭ ሽንኩርት ልጥና የኣዞ ሓረግ ቅጠል ተደቆ በለጥፍ ትንሽ ሙቅ ተደርጎ ይቀባል።[1]
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.