![cover image](https://wikiwandv2-19431.kxcdn.com/_next/image?url=https://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/8/8c/Bundesarchiv_Bild_135-S-06-03-16%252C_Tibetexpedition%252C_Landschaftsaufnahme%252C_Chumbital.jpg/640px-Bundesarchiv_Bild_135-S-06-03-16%252C_Tibetexpedition%252C_Landschaftsaufnahme%252C_Chumbital.jpg&w=640&q=50)
ቹምቢ ሸለቆ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ቹምቢ ሸለቆ በቲቤት (ቻይና) ውስጥ የሚገኝ ሸለቆ ሲሆን በሲኪም (ሕንድ)፣ ቡታንና ቲቤት መገናኛ ቅርብ ነው። በረጃጅሞች ሂማላያ ተራሮች መካከል የሚያሳልፉ ሥፍራዎች በአካባቢው አሉ።
![Thumb image](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/8/8c/Bundesarchiv_Bild_135-S-06-03-16%2C_Tibetexpedition%2C_Landschaftsaufnahme%2C_Chumbital.jpg/640px-Bundesarchiv_Bild_135-S-06-03-16%2C_Tibetexpedition%2C_Landschaftsaufnahme%2C_Chumbital.jpg)
ሸለቆው በእንግሊዝ ኃይላት ከ1896 ዓም እስከ 1900 ዓም ድረስ ተያዘ፤ የ1896ም ወረራ መጀመርያ መትረየስ የተጠቀመበት ዘመቻ ነበረ። ይህ መሬት የቲቤት ክፍያ በ1900 ዓም ከቻይና ጪንግ መንግሥት እስከሚገኝ ድረስ ተያዘ።