![cover image](https://wikiwandv2-19431.kxcdn.com/_next/image?url=https://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/8/84/Perpendicular-coloured.svg/langam-640px-Perpendicular-coloured.svg.png&w=640&q=50)
ቀጤ ነክ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ሁለት መስመሮች ቀጤ ነክ ናቸው የሚባሉት እኩል የሆኑ ጎረቤት ማዕዘኖች መፍጠር ሲችሉ ነው። ስለሆነም መስመር AB ለመስመር CD ነጥብ A ላይ ቀጤ ነክ ነው። አንድ መስመርና አንድ ጠለለል፣ ወይንም ሁለት ጠለሎች ቀጤ ነክ ሊሆኑ ይችላሉ።
![Thumb image](http://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/8/84/Perpendicular-coloured.svg/640px-Perpendicular-coloured.svg.png)
አንድ መስመር ለሌላ መስመር ቀጤ ነክ ከሆነ በሁለቱ መስመሮች መቋረጥ የሚፈጠሩት ማዕዘኖች π/2 ራዲያን ወይንም 90° ናቸው። ይህ አረፍተነገር ሲዞር ሁለት መስመሮች መገናኛቸው ላይ 90 ዲግሪ ከፈጠሩ፣ ቀጤ-ነክ ናቸው ይባላሉ።
ሁለት መስመሮች ቀጤ ነክ ከሆኑ በሂሳብ አጻጻፍ እንዲህ ይወከላሉ፦ ABCD ።
የቀጤ ነክነት ምልክት ነው።