From Wikipedia, the free encyclopedia
ሰባቱ ዝርያዎች (ዕብራይስጥ፦ שבעת המינים /ሽብዓት ሀሚኒም/) በብሉይ ኪዳን ኦሪት ዘዳግም 8፡8 የተዘረዘሩት የሀገረ እስራኤል 7 አይነት ልዩ ምርቶች ናቸው። ከነዚህም ውስጥ ሁለቱ እህሎች ሲሆኑ 5ቱ ደግሞ ፍሬዎች ናቸው።
የተዘረዘሩት ሰባቱ ምርቶች ስንዴ፣ ገብስ፣ ወይን፣ በለስ፣ ሮማን፣ ወይራ እና ማር ናቸው። ማር ሲለን በአይሁዶች ልማድ ከተምር የተሠራው ማር መሆኑ ይታመናል እንጂ በዚህ ቁጥር የንብ ማር ማለት አይደለም። ስለዚህ 7ኛው ዝርያ ተምር ሆኖ ይቆጠራል። እነዚህ 7 ዝርያዎች እስከ አሁን ድረስ በእስራኤል አበሳሰል መሃል አይነተኛ ሚና ያጫውታሉ።
በኦሪት ዘጸአት 23፡19 እና 34፡26 «የተመረጠውን የምድርህን ፍሬ በኲራት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጣ / ታገባለህ» እና እንደገና በዘዳግም 26፡2 «...አምላክህ እግዚአብሔር ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰበስበው ፍሬ ሁሉ በኲራት ውሰድ...» ቢታዘዝም፣ በአይሁዶች ልማዳዊ ሕግጋት (ሚሽና) ዘንድ ግን ይህ ትዕዛዝ ማለት ከ7ቱ ዝርያዎች የሆኑት በኲራት ፍሬዎች ብቻ ወደ ቤተ መቅደስ ማምጣት ይገባል እንደ ማለት ያደርጉታል።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.