From Wikipedia, the free encyclopedia
ሰሐራ በረሓ (አረብኛ፦ الصحراء الكبرى አል-ኩብራ ወይም ታላቁ በረሓ ማለት ነው።[1]) የዓለማችን ሰፊው ሞቃት በረሓ ነው። በዚህም ስፋቱ ከ9,400,000 ካሬ ኪ.ሜ. (3,630,000 ካሬ ማይል) በላይ ነው። በረሓው የሚሸፍነው አብዛኛውን የሰሜን አፍሪካ ክፍል ሲሆን በስፋቱም ከአውሮፓ ወይም ከአሜሪካ ጋር ይወዳደራል። ከዚህ በረሓ የሚሰፋው ብቸኛው አንታርክቲካ ሲሆን ይህም የሆነው በዝቅተኛ የዝናብ መጠን ነው። የሰሐራ በረሓ የሚያካልለው የሜዲትራኒያን ጠረፍ ጨምሮ ቀይ ባሕርን እስከአትላንቲክ ውቅያኖስ ጠረፍ ድረስ ያለውን ነው። በስተደቡብ የሳር ምድር እና የቁጥቋጦ ምድር የሆነውን ከበረሓው ጋር በሚያገናኘው የሳህል መቀነት ያዋስነዋል።
አንዳንዶቹ የአሸዋ ክምሮች እስከ 180 ሜትር (590 ጫማ) ከፍታ አላቸው።[2]
የሰሐራ በረሓ ባለፉት ጥቂት መቶ ሺህ ዓመታት ሲለዋወጥ የቆየ የአየር ሁኔታ ነበረው። በቀዝቃዛው የበረዶ ዘመን ክፍል (glacial period) ጊዜ በረሓው ከዚህም በላይ ሰፊ ነበር። በዚህ ዘመን መጨረሻ (ከ8000 ዓ.ዓ. እስከ 6000 ዓ.ዓ.) አካባቢ በርከት ያለ የዝናብ መጠን ተመዝግቦ ነበር።
የካቲት ፲፩ ቀን 1971 ዓ/ም በአብዛኛው ደቡባዊ አልጀሪያ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ጥሎ ነበር። በዚህ ዕለት ለግማሽ ሰዓት ያህል የቆየ የበረዶ ነጎድጓድ የነበረ ሲሆን ከሰዓታት በኋላ በረዶው ጠፍቷል። ይህ ዜና በተለያዩ የመገናኛ ብዙሓን ለመጀመሪያ ጊዜ በሕይወት የምናስታውሰው ዝናብ ሰሐራ በረሓ ላይ በሚል ርዕስ ሊወጣ ችሏል።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.