From Wikipedia, the free encyclopedia
ሠ ሡ ሢ ሣ ሤ ሥ ሦ ሧ
ሠውት (ወይም ሣውት) በጥንታዊ አቡጊዳ ተራ 21ኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓን በአራማያ በዕብራይስጥ በሶርያም ፊደሎች 21ኛው ፊደል "ሺን" ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል "ሺን" ተብሎ በ"አብጃድ" ተራ 21ኛ ነው።
በአማርኛ አጻጻፍ ብዙ ጊዜ "ሠውት" ከ"ሳት"(ሰ) ጋራ ሊለዋውጥ ይችላል። ቀድሞ ግን በግዕዝ የ"ሠውት" ድምጽ "ሸ" ለማመልከት ይጠቅም ነበር።
የሠውት መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የጥርስ ስዕል መስለ።
የከነዓን "ሺን" እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ የአረብኛም "ሺን" ወለደ። ከዚህ በላይ የግሪክ አልፋቤት "ሲግማ" (Σ, σ/ς) አባት ሆነ። እሱም የላቲን አልፋቤት (S s) እና የቂርሎስ አልፋቤት (С с) እና (Ш ш) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ"ሠውት" ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.