ማካቬሊ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ማካቬሊ በ 1469, ፍሎረንስ ከተማ , ጣልያን ሲወለድ , በ 1527 ሊያርፍ በቅቷል :: ከማካቬሊ በፊት በዙ ርዮቶች ቢኖሩም , የሱን ርዮት አብዮታዊ የሚያረገው ፖለቲካን ከሥነ ምግባር ነጻ ማውጣቱ ነበር :: ሥነ ምግባር (morals) በጅ የማይዳሰስ , በስንዝር የማይለካ ነው :: ሥነ ምግባር የሌለው ፖለቲካ እንግዲህ ሳይንሳዊ ፖለቲካ ሊባል ይችላል ምክንያቱም ውጤቱ ተጨባጭ ነውና ::ከማካቬሊ ታዋቂ መጽሀፎች ውስጥ , "the prince" ከፍተኝውን ቦታ ይይዛል :: ይህ መጽሀፍ ከያዛቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል :-- 1) መሪዎች ለመፈራት ና ለመወደድ መሞከር አለባቸው ብሎ ይመክራል :: ከሁለቱ አንዱን የግድ መምረጥ ካለባቸው ግን : መፈራትን መምረጥ ይሻላል ብሏል :: 2) መሪዎች ምንጊዜም ደካማ ተቃዋሚን መታገስ አለባቸው ምክንያቱም ግርግር በተነሳ ቁጥር ይህን ደካማ ቡድን በቀላሉ በመደምሰስ , ለቀሪው ህዝብ የማያሻማ ማስጠንቀቂያ መስጠት ይቻላልና :: 3)ሁለት ጎራወች ሲጣሉ , መሪዎች , ምንጊዜም ጠንካራውን ወግን መደገፍ እንዳለባቸው መክሯል :: ለዚህ ምክንያቱ : ከጥሉ በሁአላ ድሉ የጠንካራው ስለሚሆን , የደካማው ጥላቻ ምንም ለውጥ አያመጣም :: ሁለቱንም አለመደገፍ ግን , የደካማውን ጥላች ሲያተርፍ , የጠንካራውን የድል -አጥቢያ ጡንቻ በራስ ላይ ይጋብዛል :: ይህ ደግሞ ሁለት እጥፍ ኪሳራን ያመጣል ብሏል ::