ማሞ ውድነህ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ማሞ ውድነሀህሀህሀህሀህህ የቴአትር ደራሲ፥ ጋዜጠኛና ለ12 አመት የቀድሞው የኢትዮጵያ ደራሲዎች ማኅበር ሊቀ መንበር ነበሩ [1]። በአቡነ ጳውሎስ በሚመራው የሃይማኖት ኮሚቴ ውስጥ በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ሰላምን ለማምጣት ጥረት ካደረጉ ሰዎችም አንዱ ነበሩ። የ54 መጻህፍት ደራሲና ተርጓሚ የነበሩት አቶ ማሞ በማስታወቂያ ሚኒሰቴር ስር በሚታተሙ ጋዜጦችና መጽሔቶች በጋዜጠኝነት የሰሩ ሲሆን የፖሊስና እርምጃው ጋዜጣ መስራችና ተባባሪ ዋና አዘጋጅ ነበሩ፡፡ በኤርትራ ጠቅላይ ግዛት የማስታወቂያ ሚኒስቴር ተጠሪ ሆነዉ በተመደቡበት የጋዜጠኝነትና የፖለቲካ ስራ በተጨማሪ ህብረት በተሰኘዉ ሳምንታዊ የአማርኛ ጋዜጣ ዘገባዎችና ትንታኔዎች ያቀርቡ ነበር።
ባደረባቸዉ ሕመም ምክንያት በተለያዩ ሆስፒታሎች ህክምናቸዉን ሲከታተሉ የነበሩት አቶ ማሞ ዓርብ የካቲት ፳፫ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡ፀሎተ ፍትሐቱ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳዉሎስ ፓትሪያሪክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ መሪነት ተፈፅሟል፡፡ አስክሬናቸውም በደራሲ ሐዲስ ዓለማየውና ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድኅን መካነ መቃብር አጠገብ አርፏል፡፡ በቀብራቸዉ ላይ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የቀድሞዉ የአዲስ አበባ ከንቲባዎች ከንቲባ ዘውዴ ተክሉና ከንቲባ ብርሃነ ደሬሳ ተገኝተዋል፡፡[2]