![cover image](https://wikiwandv2-19431.kxcdn.com/_next/image?url=https://upload.wikimedia.org/wikipedia/commons/thumb/4/41/QueenOfEthiopia1933.jpg/640px-QueenOfEthiopia1933.jpg&w=640&q=50)
መነን አስፋው
From Wikipedia, the free encyclopedia
እቴጌ መነን አስፋው የቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ ባለቤት ነበሩ። ግርማዊ እቴጌ መነን መጋቢት 25 ቀን 1883 ዓም በወሎ ጠ/ግዛት በአምባሰል አውራጃ ልዩ ስሙ ዕጓ ከተባለው ቀበሌ ከጃንጥራር አስፋውና ከወ/ሮ ስሂን ሚከኤል ተወለዱ። እቴጌ መነን በልጅነት ዘመናቸው በእናት በእባታው ቤት መምሀር ተቀጥሮላቸው ኣማርኛ ማንበብና መፃፍ ጠንቅቀው አወቁ። በተጓዳኝ ልዩ ልዩ የቤት ባልትና ሙያዎችን ተምረው በማጠናቀቃቸው የቤት ራስ ለመባል በቅተዋል።
==
Quick Facts እቴጌ መነን አስፋው, ባለቤት ...
እቴጌ መነን አስፋው | |
---|---|
![]() | |
ባለቤት | ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ |
ልጆች | ልዕልት ተናኘወርቅ ዓፄ አምኃ ሥላሴ ልዕልት ዘነበወርቅ ልዕልት ፀሐይ ልዑል መኮንን ልዑል ሣህለ ሥላሴ |
ሙሉ ስም | ወለተ ጊዮርጊስ (የክርስትና ስም) |
አባት | አስፋው፣ የአምባሰል ጃንጥራር |
እናት | ወይዘሮ ስኂን ሚካኤል |
የተወለዱት | መጋቢት ፲፯ ቀን ፲፰፻፹፩ ዓ.ም. |
የሞቱት | የካቲት ፰ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓ.ም. |
የተቀበሩት | መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል |
ሀይማኖት | የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና |
Close
==
መነን የሚለው ቃል በዐማርኛ የሴት ልጅ ስም ሲሆን ታላቁ ምሁር ዓለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ ቀጭን ፈታይ፣ ባለሟያ፤ ወይም መልከ መልካም፤ ትክክል ፍጽምት ሕጸጽ የሌለባት ማለት እንደሆነ አፍታትተው አሥፍረውታል።[1]
(ይህ ታሪክ ነክ ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። እርስዎ ሊያስፋፉት ይችላሉ!)