መስከረም ፳፮
From Wikipedia, the free encyclopedia
በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፳፮ኛው ዕለት እና የመፀው የመጀመሪያው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፵ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ዮሐንስ ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፴፱ ዕለታት ይቀራሉ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዕምነት ተከታዮች "ዘመነ ጽጌ" ወይም "ወርኅ ጽጌ" የሚባለውን የማርያምን ስደት መታሰቢያ የ ፵ ቀን የጽጌ ፆም በዛሬው ዕለት ጀምረው ኅዳር ፮ ቀን ይፈቱታል።