ቢግ ማክ የሃምበርገር ዓይነት ሲሆን በፈጣን ምግብ ቤቱ ማክዶናልድስ የሚሸጥ ነው። ሃምበርገሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረው በ1960 ዓ.ም. በአሜሪካኑ ጅም ዴልጋቲ ነበር። ሁለት የተፈጨ የበሬ ስጋ ክቦችን፣ ሰላጣ ቅጠል፣ ዓይብ፣ ሽንኩርት፣ ፒክልስ እና ሶስት የሰሊጥ ጠፍጣፋ ዳቦዎችን ከማዋዣ የቢግ ማክ ሶስ (መረቅ) ጋር ይይዛል።
ቢግ ማክ በኣሁኑ ዘመን በአለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተዎዳጅነትን በማግኘቱ ዘ ኢኮኖሚስት የተሰኘው የሥነ ንዋይ ጋዜጣ በያመቱ ቢግ ማክ ኤንዴክስ የተባለ መረጃ ያትማል። ቢግ ማክ በያገሩ የሚሸጥበትን ዋጋ በማዎዳደር፣ የየአገሩን የኑሮ ውድነት ለማነጻጻር ይጠቀምበታል። |
|
|
ታሪክ በዛሬው ዕለት (ኤፕሪል 13, 2024 እ.ኤ.አ.):
- ፭፻፭ ዓ.ም.፣ ኢትዮጵያዊው ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ ተወለደ።
- ፲፭፻፳፬ ዓ/ም - አይፈርስ አምባ በተባለ ስፍራ ከግራኝ መሀመድ ጋር በተደረገ ጦርነት ራስ እስላም ሰገድ፣ ተክለ ኢየሱስ እና ብዙ መኳንንት ሞቱ።
- ፲፱፻፲፰ ዓ.ም.፦ ቤተ ሳይዳ (በኋላ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሆስፒታል ፣ አሁን የካቲት ፲፪ የተባለው) ሆስፒታል ተቋቋመ፡፡
- ፲፱፻፵፫ ዓ.ም. ፦ ፪ ሺህ ፻፷፰ ወታደር ያሰለፈው የኢትዮጵያ የክቡር ዘበኛ ሠራዊት፣ ቃኘው የሻለቃ ጦር ወደ ኮርያ ዘመተ። ከዘማቾቹ ማህል አንዱ የነበረው ‘የክራሩ ጌታ’ የ፶ ዐለቃ ካሣ ተሰማ "እልም አለ ባቡሩ" በሚለው ዘፈኑ ይሄንን ዕለት አወድሶታል።
- ፲፱፻፶፮ ዓ/ም - አንጋፋው የፊልም ተዋናይ ሲድኒ ፗቲዬር ‘ሊሊስ ኦፍ ዘ ፊልድ’ (Lilies of the Field) በተባለው ፊልሙ የ’ኦስካር’ ሽልማት ሲቀበል የመጀመሪያው ጥቁር አሜሪካዊ ነው።
|
|