From Wikipedia, the free encyclopedia
ሐምሌ ፲፮ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፲፮ ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፶ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፶፩ ቀናት ይቀራሉ።
፲፱፻፳፩ ዓ/ም የኢጣልያ የፋሽስት መንግሥት የሌላ ቋንቋ ወይም ባዕድ ቃላትን መጠቀምን ህገ ወጥ አድርጎ ደነገገ። (ኢትዮጵያም እንዲህ አይነት ህግ ባወጣች!!!!)
፲፱፻፵፬ ዓ.ም በጋማል አብደል ናስር የተመሠረተው የግብጽ የመኮንኖች እንቅስቃሴ በ ጄነራል ሙሐመድ ናጊብ መሪነት ንጉሥ ፋሩቅን ገለበጠ።
፲፱፻፷፮ ዓ/ም የግሪክ ወታደራዊ መንግሥት ውድቅ ሆኖ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር ኮንስታንቲን ካራማንሊስ መንግሥት እንዲመሠርቱ ተጋበዙ።
፲፱፻፺፩ ዓ/ም የሞሮኮው አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን አል ሓሳን አባታቸው ሲሞቱ ንጉሥ ሞሐመድ አራተኛ ተብለው የንጉሥነት ዘውድ ጭነው ነገሡ።
፲፰፻፹፬ ዓ/ም የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ፡ኃይለ፡ሥላሴ በሐረርጌ ውስጥ ኤጀርሳ ጎሮ ላይ ተወለዱ።
፲፱፻፺፩ ዓ/ም የሞሮኮው ንጉሥ ዳግማዊ ሀሰን በተወለዱ በ ሰባ ዓመታቸው አረፉ። ዳግማዊ ሀሰን በ ፲፱፻፶፮ ዓ/ም አዲስ አበባ ላይ የተመሠረተውን የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ከመሠሩት ሠላሳ አምስት መሪዎች አንዱ ነበሩ።
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.