From Wikipedia, the free encyclopedia
ሆተፒብሬ ቀማው ሲሃርነጅሀሪተፍ (ወይም ሰሀተፒብሬ) ላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1806 እስከ 1803 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የአመኒ ቀማው ተከታይ ነበረ። ሕልውና ከአንዳንድ ቅርስ ተረጋግጧል። ከነዚህ በተለይ የሚጠቀሰው በኤብላ የተገኘ ዱላ ቅርስ ነው፤ ይህ በኤብላ ገዥ ኢመያ መቃብር በመገኘቱ የሆተፒብሬም ስም ስላለበት ከፈርዖኑ ለኢመያ የተሰጠ ስጦታ እንደ ነበር ይገመታል።
==
==
የግብጽ ታሪክ ሊቅ ኪም ራይሆልት እንደሚያስረዳው የአመኒ ቀማው ልጅና ተከታይ ይሆናል። ስያሜው «ቀማው ሲሀርነጅሀሪተፍ» ማለት «የቀማው ልጅ ሲሀርነጅሀሪተፍ» ይመስለዋል።
በራይሆልት አስተሳሰብ፣ የሆተፒብሬ ተከታይ ዩፍኒ ሲሆን ይህ ምናልባት ወንድሙ ወይም አጎቱ ይሆናል።
ቀዳሚው አመኒ ቀማው |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን | ተከታይ ዩፍኒ |
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.