From Wikipedia, the free encyclopedia
ሀይድሮጅን
እያንዳንዱ የውሃ ሞለኪዩን ከሁለት የሃይድሮጅን አተም ና ከአንድ የኦክሲጅን አተም የተሰራ ነው። ነገር ግን እኒህ አተሞች በከፍተኛ ጉልበት ስለተጣበቁ እርስ በርሳቸውን አላቆ አተሞቹን ለማግኘት ጉልበት ያስፈልጋል። ለዚህ ተግባር የሚውሉ ብዙ መንገዶች ቢኖሩም፣ በጣም ቀላሉና ማንም ሰው እቤቱ እኒህን ጋዞች (ኦክሲጅን እና ሃይድሮጅን) ለማግኘት ሊጠቀምበት የሚችል መንገድ ቢኖር ኤሌክትሮላይሲስ ይባላል።
ጨው የሟሟበት ውሃ በቱቦወቹ ከተሞላ በኃላ፣ የኤሌክትሪክ ገመዶቹ ውሃው ውስጥ በስዕሉ በሚታየው መልኩ ይቀመጣሉ። ከባትሪው ጋር ገመዱ ሲገናኝ ውሃው አረፋ መድፈቅ ይጀምራል። ይህ ከመሆኑ በፊት ግን የቱቦወቹን አፎች በፊኛወች መዝጋት በጣም ጠቃሚ ነው። በዚህ ሁኔታ ከባትሪው ፖዚቲቭ በሚመጣው ገምድ ጎን ባለው ቱቦ ላይ የተገጠመው ፊኛ በሃይድሮጅን ጋዝ ይነፋል። በኔጌቲቩ ጎን ደግሞ ንጹህ ኦክሲጅን ፊኛውን ይሞላል። በዚህ መንገድ እኒህን ሁለት ጋዞች ከውሃ ይመረታሉ። ማስጠንቀቂያ <font color = red> ሃይድሮጅን እጅግ ተቀጣጣይ ጋዝ ስለሆነ በጥንቃቄ መያዝ አለበት! ንጹህ ኦክሲጅን እንዲሁ እሳት ሲያገኝ ቦግ ብሎ የሚቀጣጠል አደገኛ ጋዝ ነው </font>
Seamless Wikipedia browsing. On steroids.
Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.
Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.