ሃይናን

From Wikipedia, the free encyclopedia

ሃይናን

ሃይናን (ቻይንኛ፦ 海南 ወይም /ሓይናም/) በደቡብ ቻይና ባሕር የሚገኝ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ታላቅ ደሴትና ክፍላገር ነው።

Thumb
የሃይናን ሕዝቦች በኗሪ ቋንቋ፣ የ1959 ዓም ካርታ
Thumb
የሃይናን ቢጫ ፋኖስ ሚጥሚጣ

የሃይናን ትርጉም «ከባሕር ደቡብ» ነው። የሃን ቻይናውያን ሰዎች ከ118 ዓክልበ. ጀመሮ ሠፈሩበት። አሁን 84% ይቆጠራሉ። ከነርሱ ቀድሞ የኖሩበት ኗሪዎች ሊ ብሔር ወደ ደቡብ ይገኛሉ፣ 15% ናቸው። የሁላቸው መደበኛ ቋንቋ ፑቶንግኋ ቻይንኛ ሲሆን፣ ቻይናውያን ደግሞ ሚንኛ (ሃይናንኛ)፣ ሊ ብሔርም ደግሞ ሕላይኛ ይናገራሉ። ባብዛኛው የደሴት ኗሪዎች የቡዲስም ምዕመናን ሲሆኑ፣ አንዳንድ እስላም ወይም ክርስቲያን ይገኛሉ። ዋናው ሰብል ሩዝ፣ ከዚያም ኮኮነት ዘምባባቃጫአናናስቁንዶ በርበሬሻይቡናሸንኮራ አገዳጎማ ዛፍ ሁሉ ይታረሳሉ። የሃይናን ቢጫ ፋኖስ ሚጥሚጣ ለሃይናን ደሴት ብርቅዬ የቻይና ሚጥሚጣ አይነት ነው። ለማዳ እንስሶች በተለይ ፍየልበሬየውሃ ጎሽዶሮዚዪዳክዬ አላቸው።

ሃይናን በጣም ትልቅ የቱሪስም መድረሻ ሆኗል፤ በቅርብም የቻይና መንግሥት መላው ክፍላገሩ «ዓለም አቀፍ ነጻ ንግድ ክልል» እንዲሆን ለማድረግ እያቀደ ነው።

የሃይናን ባህል ስለ አበሳሰሉ ይታወቃል፤ በተለይ የበግሠርጣን፣ ዳክዬ፣ ዶሮ፣ ዚዪ፣ አሳአሳማ አሠራሮች አላቸው። «የሃይናን ዶሮ በሩዝ» የሚል አሠራር በመላው ደቡብ-ምሥራቅ እስያ በተለይም በሲንጋፖር የተወደደ ሆኗል።

በሃይናን ደሴት ብቻ የሚገኙ ብርቅዬ አትክልትና እንስሳት ዝርዮች አሉበት። በተለይም

ከአትክልት፦

  • የሃይናን ቢጫ ፋኖስ ሚጥሚጣ የCapsicum chinense አይነት
  • የሃይናን ነጭ ጥድ Pinus fenzeliana
  • የሃይናን ዝግባ Cephalotaxus hainanensis

ከእንስሳት፦

  • የሃይናን ጸጉራም ትድግ Neohylomys hainanensis
  • የሃይናን ቆቅ Arborophila ardens
  • የሃይናን ጣዎስ Polyplectron katsumatae
  • የሃይናን ጥቁር-ጉትያ ጊቦን ጦጣ Nomascus hainanus
  • የሃይናን መንትሌ Lepus hainanus
  • የሃይናን ነብር-ድመት Prionailurus bengalensis alleni የነብር-ድመት ንዑስ ዝርያ ነው።
  • የሃይናን ቅጠል ተንጫጪ ወፍ Phylloscopus hainanus

Wikiwand in your browser!

Seamless Wikipedia browsing. On steroids.

Every time you click a link to Wikipedia, Wiktionary or Wikiquote in your browser's search results, it will show the modern Wikiwand interface.

Wikiwand extension is a five stars, simple, with minimum permission required to keep your browsing private, safe and transparent.