የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ
From Wikipedia, the free encyclopedia
የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ፳ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሲሆን ከሰኔ ፭ እስከ ሐምሌ ፮ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. በብራዚል ይካሄዳል።[1] ብራዚል ይህን ውድድር ስታዘጋጅ ይሄ ሁለተኛ ጊዜዋ ነው። ፊፋ የ2014 እ.ኤ.አ. ውድድር በደቡብ አሜሪካ እንደሚካሄድ በ2007 እ.ኤ.አ. ካወጀ በኋላ ብራዚል ያለማንም ተቀናቃኝ አዘጋጅ አገር ሆና ተመርጣለች።
Quick Facts
የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ |
|
---|---|
ይፋዊ ምልክት
|
|
የውድድሩ ዝርዝር | |
አስተናጋጅ | ብራዚል |
ቀናት | ከሰኔ ፭ እስከ ሐምሌ ፮ ቀን |
ቡድኖች | ፴፪ (ከ፭ ኮንፌዴሬሽኖች) |
ቦታ(ዎች) | ፲፪ ስታዲየሞች (በ፲፪ ከተማዎች) |
← 2010 እ.ኤ.አ. 2018 እ.ኤ.አ. → |
Close
የ፴፩ አገራት ብሔራዊ ቡድኖች ከጁን 2011 እ.ኤ.አ. ጀምሮ የተካሄዱ የማጣሪያ ውድድሮችን በማለፍ ከብራዚል ጋር በመጨረሻው ውድድር ላይ ለመሳተፍ በቅተዋል። በጠቅላላው ፷፬ ጨዋታዎች በ፲፪ ከተማዎች ውስጥ በሚገኙ አዲስ የተገነቡ ወይም የተሻሻሉ ስታዲየሞች ይከናወናሉ። በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎል ላይን ቴክኖሎጂ በጥቅም ላይ ውሏል።[2]
በ1930 እ.ኤ.አ. ከተካሄደው የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ጀምሮ ሁሉም የዓለም ዋንጫ ሻምፕዮን አገራት (ብራዚል፣ አርጀንቲና፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሣይ፣ ጀርመን[ማስታወሻ 1]፣ ኢጣልያ፣ እስፓንያ እና ኡራጓይ) በዚህ ውድድር ውስጥ ተሳታፊ ናቸው። ከዚህ በፊት በደቡብ አሜሪካ የተዘጋጁትን ዋንጫዎች እንዳለ የወሰዱት የደቡብ አሜሪካ ቡድኖች ናቸው።[3]