ኢትዮጵስት በዓለም ዙሪያ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ፅኛዥሬኞ ኢትዮጵስት በዓለም ዙሪያ የኢትዮጵያ ጥናት ፡ ይህ ጥናት አጠቃላይ የሆነ የኢትዮጵያ የታሪክ ፣ የጆግራፊ፣ የዘር፣ የቋንቋ፣ የስነፅሁፍ፣ የባሕል፣ የተፈጥሮ ሐብት፣ የኤኮኖሚ፣ የፖለቲካና የሶሻል፣ ጥናቶችን ያጠቃልላል። ይህ ነጻ የሆነ ሳይንሳዊ ጥናት በቅርቡ ተጠናክሮ የቀጠለ ቢሆንም በቅድመ ጥናቶች የተደረጉ ስራወች እንደሚያሳዮት ጥናቶች የተከሃዱት ባጠቃላይ ፖቶሎጅካል የታሪክ፣ የቋንቋ፣ የባህልና በሀገሪቱ የሚኖሩ ጎሳወችን በተመለከተ ነበር። በመጀመሪያ የኢትዮጵስት ጥናተቶች የወጡት በ17ኛዉ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ሲሆን በ20ኛዉ ክፍለ ዘመን በአዉሮፓዉያን ቋንቋ በመጀመሪያ ጊዜ በኢጣሊያንኛ ከዚያም በፈረንሳይኛና በእንግሊዝኛ ስለትዮጵያ ጥናታዊ ጽሑፎች ብቅ ማለት ጀመሩ። ስለዚህም እንደምሳሌ የሚጠቀሰዉ ‘የኢትዮጵያ ጥናት‘ በሚል /studi etiopici; etudes ethiopiennes; Ethiopian studies/ በኢጣሊኛ ቋንቋ የሚታተም ጽሑፍ ነበር። የኢትዮጵስት የኢትዩጵያ ጥናት የሚለዉ ሀሳብ በተለይም ከመጀመሪያዉ ዓለም አቀፍ የኢትዮዽያ የጥናት ኮንፍረስ በሁዋላ ታዋቂ ሆኗል። {1959 በሮም ኢጣሊ} በአሁኑ ጊዜ ከ16 ያላነሱ ኮንፍረንሶች ተካሂደዋል። በነዚህም ኮንፍረንሶች ላይ አያሌ ኢትዮጵስት ምሁራን በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ብዛት ያላቸዉ ጥናቶችን አቅርበዋል። በመካከለኛዉ ዘመን ኢትዮዽያ የሚባለዉ አካባቢ በተጨማሪ ‘የቅዱስ ዮሐንስ የክርስቲያኖች ሀገር በሚል በብዛት ይታወቅ ነበር። እንዲሁም አቢሲንያ በመባልም ይታወቃል። በ4ኛዉ ክፍለዘመን ክርስትና በአክሱም በመስፋፋቱ በኢትዮጵያና በኗሪወቿ ለይ ከፍተኛ ለዉጥ አስከትሏል። ለዉጭዉም ዓለም ትኩረትን አሳይቷል። ስለሆነም የቤዛንቲያን፣ የአርሚያን፣ የሮማዉያን ፣የፖርትጋል ኤፔስ ኮፖሳት በ6ኛዉ ክፍለዘመን በኢትዮዽያ ጉብኝቶችን አድርገዋል።
አረቦች ከኢትዮዽያና ከሕዝቦቿ ጋር በጥሩ ሁኔታ ይተዋወቃሉ። ይሄም እስልምና ከመፈጠሩ በፊት በነበረዉ የንግድና የባህል ልዉዉጦችና ግንኙነቶች ነበር። ከእስልምና በሁዋላም ቢሆን ችግር ባጋጠማቸዉ ጊዜ የመሐመድ ተከታዮች በስደት ወደ ኢትዮጽያ መጥተዋል። የአረብ የታወቁ የጆግራፊና የታሪክ ጽሐፊወች ያኩቢ፣ ማሱዲ፣ኢባን ሀያካሊያ፣ ያኩዬታ፣ ኢባን ሱኢዳ ከ9ኛዉ እስከ 14ኛዉ ክፍለዘመን በተደረጉ የጥናት ስራወቻቸዉ በጣም ከፍተኛ ታሪካዊ ዋጋ ያላቸዉና ስለ መካከለኛዉ ዘመን ኢትዮጽያ ታሪክ፣ ጆግራፊ፣ ኤትኖግራፊ የተጻፉ ስራወቻቸዉ ከፍተኛ የታሪክ ማጣቀሻወች ናቸዉ።
በመካከለኛዉ ዘመን አዉሮፓዉያን በተከታታይ ወደ ኢትዮጽያ ትኩረት አድርገዉ ነበር። ይሄዉም በ12ኛዉ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ነዉ። ለዚህም ዋናዉ ምክንያት በዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ የእስልምና መስፋፋት ስለነበር ይህንን ለመቋቋም በሚደረገዉ ትግል አጋዠ ለማድረግና የጋራ ግንባር ለመፍጠር ነበር። በዚህ የእስልምና መስፋፋት ዘመን ይህች የቅዱስ ዬሐንስ የክሪስታኖች ሀገር በሚል የምትታወቀዉ ኢትዮጵያ የበኩሏን አስተዋጦ አድርጋለች። ኢትዮጵያ በዚያን ጊዜ በእየሩስዓለምና በሮም የኢንፎርሜሽን ሴንተሮች ቤተክሪስታኖች ነበሯት።እንዲሁም በዚያን ጊዜ ካይሮ ታለቅ የንግድ ሴንተር ስለነበረች ኢትዮጵያም ታለቅ የንግድ ግንኙነት ስለነበራት እንደ ኢንፎርሜሽን ሴንተር ትገለገልበት ነበር።
16ኛዉና17ኛዉን ክፍለዘመን አዲሱ የኢትዮጵያ ጥናት የታሪክ ዘመን በማለት መጥራት ይቻለል። ይሄዉም የፖርቱጋሎች ወደ ኢትዮጵያ መምጣትና እንዲሁም የጽሐፋቸዉ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸዉ የታሪክ ማስታወሻወችና መጽሐፍት ናቸዉ። ከነዚህም መካከል፡
አለባሪሽ ‘እዉነተኛ ታሪክ ስለ ቅዱስ ዩሐንስ የቅዱሳን ሀገር’ {1540}
ካሽታኑዩዝ “የፖርትጋሎች ጉዞ ታሪክ በአቢሲኒያ’ {1564} እንዲሁም ፖርቱጋልን ያገለግል በነበተዉ የእስፓኒሽ ተወላጅ ፓይሱ ‘የኢትዮጽያ ታሪክ’ በመጀመሪያ አጠቃሎ የታተመዉ በ1945/46 እነዚህ የፖርቱጋል አገር ጎብኝወችና ታርክ ጸሐፊወች ኢትየጵያንና የሕዝቦቿን ታሪክ ለአዉሮፓዉያን በማስተዋወቅ ታላቅ ሚና ተጫዉተዋል ወይም ቀደምትነት ነበራቸዉ።
በ17ኛዉ ክፍለዘመን መጨረሻ በአዉሮፓና በሌሎችም አገሮች ስለኢትዮዽያ ስለመሬቷ ለምነት፣ ስለሕዝቦቿ አኗኗር፣ ስለቋንቋዋና ባሕሏ ብዙ ጥናታዊ ስራወች ተሰርተዋል። ሆኖም እነዚህ ስራወች ብዙወቹ ስተቶች ያሉባቸዉና ያልተስተካከሉ ነበሩ።
በአዉሮፓ የኢትዮጵያ ጥናት መስራች ተብሎ የሚታወቀዉ ኢትዮጵስት ጀርመናዊዉ ተመራማሪ ፔሩ ሉዶልፍ {1624-1704} ነዉ። የሱ ስራወችም የኢትዮጵያ ታሪክ መዝገበ ቃላቶች ናቸዉ ማለት ይቻላል። ስራወቹም በተለያዩ የታሪክ ክፍሎች ላይ የተመሰረቱ ናቸዉ። ለምሳሌ ኤትኖግራፊ/ሕዝብ /፣ ጆግራፊ፣ ታሪክ፣ ፍልስፍና ሌሎችም ነበሩበት። የእሱ የኢንፎርሜሽን ምንጭም ለብዙ ዓመታት በሮም ይኖሩ የነበሩት ኢትዮጵያዊ ቄስ መነኩሴ ግሪጎሪ ናቸዉ።
ፔሩ ሉዶልፍ ታላላቅ ስራወቹን በፍራንክፈርት አሳትሟል ከእነዚህም መካከል።
‘የኢትዮጵያ ታሪክ’ {1681}፣ ‘አጠቃላይ የሆነ እርማት ከኢትዮጵያ ታሪክ’ {1691}፣ ‘የግዝ ቋንቋ ሰዋሰዉ /ግራመር/ {1661-1702}፣ ‘የአማርኛ ሰዋሰዉ /ግራመር/ና መዝገበ ቃላት’ {1698}፣ ‘የግዝ ስነጽሑፍ መስፋፋትና መዝገበ ቃላት’ {1699} የሚሉ ናቸዉ።
የፔሩ ሉዶልፍ መጸረሐፍትና ስራወች በፈረንሳይ፣ በእንግሊዝና በሌሎችም የአዉሮፓዉያን ቋንቋወች ተተርጉመዉ ነበር። ለረጅም ጊዜም እንደ ቋንቋ መዝገበ ቃላትና የታሪክ መማሪያነት አገልግለዋል። ‘የኢትዮጵያ ታሪክ’ የሚለዉ መጽሐፍ በራሽያን ቋንቋ ተተርጉሞ ለታላቁ ፔትሮስ /ጴጥሮስ/ አንደኛ በስጦታ ተሰጧቸዉ ነበር።
ከፔሩ ሉዶልፍ በሁዋላ በኢትዮዽያ ጥናት ላይ መዳከም ታይቶ የነበር ቢሆንም በ18ኛዉ ክፍለዘመን መጨረሻና በ19ኛዉ ክፍለዘመን መጀመሪያ እንግሊዛዊያን ዠ- ቦርዩስ {1730-1794} እና ገ- ሶልት {1780-1827} አዲሱን የኢትዮጵያ ጥናት ጀመሩት። እረጅም ጊዜ የፈጀ ጉብኝትም አደረጉ ብዙ ጥናቶችንም አቀረቡ ቦርዩስ አባይ ከጣና ይፈልቃል አለ። በ1790 ጉብኝቱ በጻፈዉ ጽሑፍ ብዙ የጆግራፊ፣ የኤትኖግራፊ፣የታሪክ ሪኮርዶችን ለመጥቀስ ሞክሯል። ብዙ የኢትዮጵያ የጅ ጽሑፎችንም ሰብስቧል። በሁዋላም ለኦክፎርድና ለማንችስተር ዩንበርስቲወች ሰጧቸዋል። ሶልት ሁለት ጊዜ ያህል ኢትዮጵያን ጎብኝቷል {1805-1810} በስራወቹ ትኩረት ያደረገዉ በሰሜን ኢትዮዽያ በተለይም በአክሱም በሚገኙት ሐወልቶችና ጸረሑፎች ላይ ነበር። በ19ኛዉ ክፍለዘመን ኢትዮጵስትና የኢትዮጵያ ጥናት በፍጥነት ተቀይሯል። ብዙ ጥናታዊ ተቋማትም ተመስርተዋል። በአዉሮፓ በሚገኙ የኢትዮጵያ ቅርሶች ላይም መሰረታዊ የሆኑ ሳይንሳዊ ምርምሮችና ጥናቶች ተካሂደዋል። እንዲሁም ብዙ ጥናታዊ ጉዞወች ወደ ኢትዮዽያ ተደርገዋል። በተደረጉትም ጉዞወች በርካታ ጥናቶች ተካሂደዋል። ስለ ሴሜትክና ኩሸቲክ ቋንቋወች ጥናቶች ተደርገዋል። በ19ኛዉ ክፍለዘመን አጋመሽ ጀርመናዊዉ ተመራማሪ አ-ዲሊማን መሪነት ስለ ጥንታዊ ኢትዮጵያ ታሪክ፣ ስለ መካከለኛዉ ዘመን ኢትዮጵያ ታሪክ፣ ስለግዕዝ ቋንቋ ሰዋሰዉ /ግራመር/ ስለ ሊቶግራፊና ሌሎችም ጥናቶችን አካሂደዋል። በነዚህና በመሳሰሉት ስራወች ላይ ከፍተኛ አስተዋጾ ያደረጉ ተመራማሪወችም፡ ፈ- ፐሪቶሪዮስ፣ ኦ- ሙቲቦክስ፣ ከ- ቢትሊድ፣ እንዲሁም አዉስትሪያዊዉ ኤ- ሊትማን ይገኙበታል።ኤ- ሊትማን በ1905፣1906 በአክሱም የተካሄደዉን የአርኪኦሎጅ ምርምርና የተመራማሪወች ቡድን መርቷል። የዚህ ጥናት ዉጤት በአራት ቶሞች በ1913 ታትሟል። ብዙ የአርኪኦሎጅና የኢፖግራዊ ስራወች ስለ ጥንታዊ ኢትዮጵያ ይዟል። ኤ- ሊትመን {1910-1915} ሌላ የጥናት ቡድንም በኢትዮጵያ መርቷል። ይህ የጥናት ቡድን ስለስነጽሑፍና ስለፍልስፍና ጥናት ያደረግ ሲሆን፤ በተለይ በትግሬኛ ቋንቋ ላይም ጥናት አካሂዷል። ኤ- ሊትማን በብራሴል ዩንበርስቲ በሴሚቶሎጅ ፋኮሊቴት ስለ ኢትዮጵያ ያስተምር ነበር።