ናይጄሪያ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ናይጄሪያ በይፋ የናይጄሪያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ በምዕራብ አፍሪቃ የምትገኝ አገር ናት። በሕዝብ ብዛትም ከአፍሪቃ አንደኛ ናት። ከቤኒን ፣ ቻድ ፣ ካሜሩን ፣ ኒጄር ፣ እና ከጊኒ ባሕረ ሰላጤ ጋር ድንበር ትካለላለች። በናይጄሪያ ውስጥ ትልቁ ብሔሮች ሀውዛ ፣ ኢግቦ እና ዮሩባ ናቸው። ግማሹ ሕዝብ እስላም ሲሆን ሌላው ግማሽ ደግሞ የክርስትና እምነት ይከተላል። ትንሽ የሕዝቡ ክፍልም ባህላዊ ሃይማኖቶችን ይከተላል።
የናይጄሪያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ብሔራዊ መዝሙር: Arise, O Compatriots | ||||||
ናይጄሪያ በአረንጓዴ ቀለም
|
||||||
ዋና ከተማ | አቡጃ | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | እንግሊዝኛ | |||||
መንግሥት ፕሬዝዳንት ምክትል ፕሬዝዳንት |
ፕሬዝዳንታዊ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ሙሐማዱ ቡሐሪ የሚ ኦሲንባጆ |
|||||
ዋና ቀናት 1914 እ.ኤ.አ. መስከረም ፳፩ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓ.ም. መስከረም ፳ ቀን ፲፱፻፶፮ ዓ.ም. |
የሰሜንና ደቡብ ናይጄሪያ ውህደት የነፃነት አዋጅ የሪፐብሊክ ምሥረታ |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) ውሀ (%) |
923,768 (32ኛ) 1.4 |
|||||
የሕዝብ ብዛት የ2010 እ.ኤ.አ. ግምት |
155,215,573[1] (8ኛ) |
|||||
ገንዘብ | ናይራ (₦) | |||||
የሰዓት ክልል | UTC +1 | |||||
የስልክ መግቢያ | 234 | |||||
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ | .ng |
የሳይንስ ጥናት እንደሚያሳየው ናይጄሪያ ከ፱ሺህ ዓመታት ከክርስቶስ ልደት በፊት ጀምሮ ነዋሪዎች እንደነበሩባት ያሳያል።[2] በቤንዌ እና ክሮስ ወንዞች አካባቢ ያለው ሥፍራ የባንቱ ፍልሰቶች መነሻ እንደ ነበረ ይታመናል።
የናይጄሪያ ስም ከኒጄር ወንዝ ነው የተወሰደው። ናይጄሪያ በአፍሪካ በሕዝብ ቁጥር አንደኛ ስትሆን ከዓለም ደግሞ ሰባተኛ ናት። የናይጄሪያ ኢኮኖሚ በዓለም ላይ በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉት ኢኮኖሚዎች ይመደባል። የዓለም አቀፍ ገንዘብ ፈንድ እንደሚገምተው የናይጄሪያ ኢኮኖሚ በ2011 እ.ኤ.አ. በ8% ያድጋል።[3]