ትራምፔት
From Wikipedia, the free encyclopedia
ትራምፔት ዘመናዊ የትንፋሽ የሙዚቃ መሣሪያ ነው። ይህ መሣሪያ ከነሐስ የሚሠሩ የሙዚቃ መሣሪያዎች ውስጥ ከፍተኛውን የኖት ሬንጅ የሚያወጣ ነው። መሣሪያውን ለመጫወት በከንፈር መንፊያውን በመያዝ ወደትራምፔቱ ቱቦ ውስጥ አየር በተወሠነ የኃይል መጠን ማስገባትን ይጠይቃል። በመቀጠልም በመሣሪያው ወገብ ላይ የሚገኙትን ቁልፎች በእጅ ጣት በመነካካት ውስጥ ያለውን ድምፅ ፈጣሪ አየር ሞገድ መስጠት ይቻላል። ይህም የሚፈጠረውን ድምፅ ውፍረት እና ቅጥነት ለመቀያየር ይረዳል።