ቴዲ አፍሮ
ኢትዮጵያውያን ዘፋኝ / From Wikipedia, the free encyclopedia
ቴዲ አፍሮ (Teddy Afro) ዕውነተኛ ስሙ: ቴዎድሮስ ካሳሁን ሲሆን ከዘመናችን ወጣት ኢትዮጵያውያን ዘፋኞችና አቀንቃኞች ሁሉ እጅግ ዝነኛ ነው። ቴዲ ለጃማይካዊው ሬጌ ኮከብ ቦብ ማርሊ የዘፈነለት የሬጌ ሙዚቃው በዓለም ዙሪያ እንዲታወቅ ያደረገው ሲሆን በተለይ ለኃይሌ ገብረ ሥላሴ ና ለሌላኛው የኦሊምፒክ ጀግና ቀነኒሳ በቀለ በኦሊምፒክስ ካሸነፉ በኋላ ያወጣቸው ወቅታዊ አልቡሞቹ ይበልጥ ታዋቂ አርገውታል። ቴዲ አፍሮን በጣም ታዋቂ ያደረግው 'ያስተሰርያል' የተባለው አልበሙ ሲሆን ስለ ፍቅር ፣ መቻቻል ፣ ህዝብ ስሜት እንዲሁም ስለመንግስታት እና ስለ ተቃዋሚዎች በፍቅር ለሃገር እድገት መስራት ዘፍኖአል። ዘፈኖቹ ብስል እና ጠንካራ ናቸው። ቴዎድሮስ ካሳሁን ከድምፃዊነትም በተረፈ የግጥምና ዜማም ደራሲ ሲሆን ከራሱ ስራዎች በተጨማሪ ለተለያዩ ድምፃዊያን የግጥም እና ዜማ ድረሰቶችን አበርክቷል። ቴዎድሮስ ካሳሁን ሐምሌ 7 1968 በአዲስ አበባ ተወለደ። የትምህርት ደረጃ 12+ {{መለጠፊያ:Infobox musical artist|en}}
የዚህ መጣጥፍ የማያደላ ዝንባሌ ያለው ሁናቴ መኖሩ አጠያያቂ ጉዳይ ነው። (መግለጫውን በውይይት ገጽ ላይ ይፈልጉ።) |
ይህ መጣጥፍ ምንም ዓይነት የዋቢ ምንጮች አያካትትም። እባክዎን ተገቢ ምንጮን በመጥቀስ ያሻሽሉት። |