ሶቅራጠስ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ሶቅራጠስ (470 ዓ.ዓ. - 399 ዓ.ዓ.) የነበረ ዋና የጥንት ግሪክ ፈላስፋ እና አስተማሪ እንዲሁም የምዕራቡ አለም ፍልስፍና መስራች ነበር። ሶቅራጥስ በግሪክ ዋና ከተማ አቴንስ ይኖር ነበር። የሶቅራጥስ ጥናት የሰው ልጆች እንዴት ያስባሉ? በሚለው ጥያቄ ላይ ያጠነጠነ ነበር። በሌላ ጎን የሶቅራጠስ ዘዴ የሚባለውን አይነት የምርምር መንገድ በመፍጠሩም ይጠቀሳል። ማለት ከአንድ ጥያቄ ተነሰቶ ወደ ጠለቅ ያለ ጥያቄ በመሻገር ነገሮችን ከስረ መሰረታቸው ለመረዳት መሞከሪያ ዘዴ ሲሆን በዘመኑ እንግዳና የራሱ የፈላስፋው ዋና ፈጠራ ነበር።
አንድ ሰው እንዴት ሰናይ (ጥሩ) ሊባል ይቻላል በሚለው ጥያቄም ዙሪያ አስተዋጽዖ በማድረግ የሥነ ምግባር መስራችም ነው። የሶቅራጠስ አስተሳሰብ ዘዴወች ለምዕራቡ አለም ማደግ ባደረጉት አስተዋጽዖ እንዲሁም በፕላቶ እና አሪስጣጣሊስ ሰርጾ የምዕራቡን አለም አስተሳሰብ በመቀየራቸው፣ በአሁኑ ዘመን ይሄ ፈላስፋ የምዕራቡ አለም ፍልስፍና አባት በመባል ይታወቃል።