ሶማሊላንድ
From Wikipedia, the free encyclopedia
ሶማሊላንድ እውቅና ያልተሰጠው በስራው ግን እንደ አንድ ልዑላዊ ሃገር የሚንቀሳቀስ በአፍሪካ ቀንድ በሰሜን ምስራቅ ሶማሌ የሚገኝ አካል ነው። ግንቦት ፲ ቀን ፲፱፻፹፫ ዓ/ም፥ የሶማሊላንድ ሕዝብ ነጻነቱን አውጆ ከሶማሌ ፲፰ ክፍለ ሀገራት ፭ቱን አካቶ ይዟል። ይህም በጅቡቲ፣ በኢትዮጵያ፣ በቀድሞው የጣልያን ሶማሊላንድና በአደን ባሕረሰላጤ የሚካለለውን ፻፴፯ ሺ ፮መቶ ካሬ ኪሎሜትር የሚሸፍነውን ቦታ ከሞላ ጎደል ይሸፍናል። የሶማሊላንድ ዋና ከተማ ሃርጌሳ ነው።
Quick Facts Somaliland ሶማሊላንድ ...
Somaliland |
||||||
---|---|---|---|---|---|---|
|
||||||
ዋና ከተማ | Hargeisa | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | ሶማልኛ | |||||
መንግሥት ፕሬዚዳንት |
አህመድ ሞሐመድ ሞሐሙድ |
|||||
የመሬት ስፋት አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.) |
137,600 km2 |
|||||
ገንዘብ | ሶማሊላንድ ሺሊንግ | |||||
የሰዓት ክልል | UTC -+3 | |||||
የስልክ መግቢያ | +252 |
Close
እውቅና ባያገኝም አካሉ ሳይዋዥቅ እንደ መንግሥት እየሠራ ይገኛል። በመስከረም ፲፰ ቀን ፲፱፻፺፰ ዓ/ም በተደረገው የከተሞች የሊቀመንበርና የሕዝብ ተወካዮች ምርጫ ኡዱብ ፓርቲ ሲያሸንፍ በተለያዩ ታዛቢዋ ትክክለኛና ነጻ ምርጫ እንደ ነበር ዘገባ ቀርቧል። ይህም ሶማሊላንድ ላቀረበችው የእውቅናው ጥያቄ ድጋፍ ይሰጣል የሚሉ ወገኖች አሉ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |